ስለ እኛ
ቁቤ ቲቪ ተራማጅና ፈጠራ ላይ ተመርኩዞ በመጋቢት 19/2023 አ.ኤ.አ የተመሰረተ በመዝናኛ ትምህርታዊና የመረጃ ይዘቶች ላይ የሚሰራ የመገናኛ ብዙሀን ፕላትፎርም ነው። ቁቤ ቲቪ በ2035 እ.ኤ.አ በኢትዮጵያ እና ምስራቅ አፍሪቃ መሪ የሚዲያ ተቋም ለመሆን ጠንካራ ራዕይ ይዞ ተመስርቷል።
በቀጠናው የላቀ ጥራት አዝናኛና መረጃን የሚያስጨብጥ ይዘት አስፈላጊነትን የሚረዳው ቁቤ ቲቪ የታሪክ ነገራ፣ የብሮድካስትና ዲጂታል ሚዲያን ክፍተት ለመሙላት ተቋቁሟል። እውነት ላይ የተመሰረተ ጋዜጠኝነት፣ የባህል ውክልና ትምህርት አዘል የመዝናኛ አማራጭ የህዝብ ድምፅና ታማኝ የመረጃ ምንጭ ለመሆን በትጋት ይንቀሳቀሳል ።
ቁቤ ቲቪ ከጀምሩ አንስቶ በጥልቀትና በስፋት መልከ ብዙ ይዘቶችን በማዘጋጀት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ ላሉ ተመልካቾቹ በጥራት መድረስ ችሏል። በሳተላይት ስርጭት፣ በዲጂታል ፕላትፎርሞች እና በማህበራዊ ሚዲያ ትምህርታዊ ዝግጅቶችን፣ ጥልቅ ውይይቶችን፣ ማራኪና ሳቢ ታሪኮችን በማቅረብ ከሚሊዮኖች ጋር ሲገናኝ ቆይቷል።
ጣቢያችን ቁቤ ቲቪ የሚዲያን ለውጥ የማምጣት፣ ማህበረሰብ የማነጽ የማስተማርና የማዝናናት አቅምን ይረዳል። በጋዜጠኞች፣ ይዘት ፈጣሪዎች፣ የካሜራ ባለሙያዎች፣ እና ኤዲተሮች የተደራጀው የባለሙያ ቡድናችን ሐቀኛ አካታችና ጥራት ያለው ይዘት ለተመልካች ለማድረስ ያለድካም በትጋት ይሰራል።
በላቀ የጋዜጠኝነትና የታሪክ ነገራ ስልት መረጃ በመስጠት፣ በማስተማር፣ አዝናኝ ይዘቶችን በማቅረብ ከጊዜ ጋር ከፍ እያልን እንሄዳለን።
መስራች
ሙባረክ በሺር
የቁቤ ቲቪ መስራች
ቁቤ ቲቪ በሙባረክ በሺር ተመሰረተ። ሙባረክ በሺር ልምድ ያለው ጋዜጠኛ፣ የሚዲያ ስራ ፈጣሪ እና የዲጂታል ይዘት ፈጣሪ ነው። በጋዜጠኝነት፣ ኤዲቲንግ እና የሚዲያ ፕሮዳክሽን ልምድና ክህሎት ያለው ሙባረክ እንደ FiB TV እና Hamilton TV ያሉ የሚዲያ ተቋማት ውስጥ አገልግሏል። የመጀመርያ ዲግሪውን በኮምፒውተር ሳይንስ ከሀረማያ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪውን ደግሞ በፕሮጀክት ማኔጅመንት ከአድማስ ዩኒቨርሲቲ አግኝቷል።
ሙባረክ በዲጂታል ጋዜጠኝነት፣ በይዘት ፈጠራ እና ብሮድካስቲንግ ሚዲያ ያለው ልምድና ክህሎት ቁቤ ቲቪን ተዓማኒ ዜናዎች የሚያደርስ፣ የመዝናኛ ትምህርታዊና የመረጃ ይዘቶችን የሚያቀርብ ፕላትፎር እንዲያደርግ አግዞታል። ሚዲያውን በመራበት ሂደትም በአዳዲስ ፈጠራና ተደራሽነት በኢትዮጵያና ምስረቅ አፍሪቃ አዲስ መልክና ገጽታ ያለው ተቋም እየገነባ ነው።
ራዕያችን
በ2035 በጋዜጠኝነት መዝናኛና ትምህርታዊ ይዘት አዲስ ቅርፅ ያለው በኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ መሪ የሚዲያ ተቋም መሆን፣
ተልዕኳችን
- ተዓማኒ ያልተበረዘ እና አካታች የዘገባ ሽፋን መስጠት
- መረጃ የሚያስጨብጡና የሚያንጹ ጥራት ያላቸው ትምህርታዊ ይዘቶችን ማዘጋጀት
- ብዝሃ ባህልና ማንነትን የሚያሳዩና የሚያስተዋውቁ የመዝናኛ ዝግጅቶችን ማቅረብ
- በሚዲያ ፕሮዳክሽን እና ታሪክ ነገራ ዘርፍ አዳዲስ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ግብዓቶችን መጠቀም
የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካን የሚዲያ እጣፈንታ ለመቀየር በምናደርገው ጉዞ አብረውን ይሁኑ !